ደንቦችና ሁኔታዎች እና የግላዊነት ፖሊሲ

1. ስምምነት

ይህ ስምምነት የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የሐበሻቪው አገልግሎቶችን ሰብስክራይብ ለማድረግ፣ ለማግኘት ወይም ለመጠቀም የሚፈልግ ተጠቃሚ ሊያውቃቸው የሚገቡ ደንቦችና ሁኔታዎችን ይዘረዝራል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በዚህ ስምምነት መሠረት የሚያቀርባቸው አገልግሎቶች ተጠቃሚው ለአገልግሎቶቹ መክፈል የሚገባውን ክፍያ ከከፈለ በኋላ የሚያገኛቸው ናቸው፡፡ ተጠቃሚው እነዚህን አገልግሎቶች ለማግኘትና ለመጠቀም በቅድሚያ እነዚህን ደንቦችና ሁኔታዎች መቀበል ይኖርበታል፡፡

2. አገልግሎቶቹ

ሐበሻቪው አይፒቲቪ ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር፣ “ሐበሻቪው” በሚል የንግድ ስያሜ በእነዚህ ሳይወሰን እንደ ምስልና ድምጽ ፕሮግራሞች፣ ፊልሞች፣ የሙዚቃ ቪዲዮዎች፣ ሊኒየር የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ ልዩ ዝግጅቶች፣ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች፣ ማስታወቂያዎች እና ሌሎች የምስልና ድምጽ ፕሮግራሞች (ይዘት) ያሉትን የዲጂታል ይዘት በዋጋና በዚህ ስምምነት ውስጥ በተዘረዘሩት ደንቦችና ሁኔታዎች መሠረት በኢንተርኔት አማካይነት የመዝናኛ አገልግሎቶች (አገልግሎቶች) የሚያቀርብ ድርጅት ነው፡፡ ሐበሻቪው አይፒቲቪ ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለእርስዎ የሚሰጠው ውስን የመጠቀም መብት ለብቻ ያልሆነ፣ የማሰራጫና አገልግሎት የመስጫው ፈቃድ ከእርስዎ ወደ ሌላ ሰው የማይተላለፍና የማይዘዋወር፣ ይህንን መካን-ድር የማግኘት፣ የመጠቀምና ሰብስክራይብ ያደረጓቸውን ጣቢያዎች በሦስት (3) የሐበሻቪው የቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የንግድ ምልክት የተደረገባቸው መሳሪያዎች የመመልከት መብት ነው፡፡ እነዚህን ደንብና ግዴታዎች በጥብቅ በማክበር በማንኛውም ጊዜ በኢንተርኔት አማካይነት ከመካነ-ድሩ ጋር በመገናኘት (ወይም ባለቤትነቱ ወይም ኃላፊነቱ የእርስዎ በሆነ አግባብነት ባለው በሌላ መሣሪያ) የመመልከት መብት ይሰጥዎታል፡፡ አንድ ተጠቃሚ በማንኛውም በተፈቀደለት መሣሪያ የሐበሻቪውን አገልግሎቶች ማግኘት የሚችለው በአንድ አይፒ አድራሻ ብቻ ነው፡፡ የመጠቀሚያ አካውንቶችን ለጋራ መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ የመካነ-ድሩን ማንኛውም ክፍል ወይም ማንኛውንም ፊልም ወይም በመካነ-ድሩ ላይ የሚገኝ ሌላ የምስል- ወድምጽ ወይም ደጂታል ሥራዎችን ለሕዝብ ማሳየት አይፈቀድም፡፡ በመካነ-ድሩ ላይ የሚገኘውን ይዘት (“የመካነ-ድሩ ይዘት”) እና ሐበሻቪው አይፒቲቪ ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር መካነ-ድሩን ለማቅረብ የሚጠቀምበትን ሶፍትዌር (“የመካነ-ድሩን ኮድ” ጨምሮ) በማንኛውም ሌላ ወይም አግባብነት በሌለው መንገድ መካነ-ድሩን መጠቀም በጥብቀ የተከለከለ ነው፡፡ የመካነ-ድሩ ይዘትና የመካነ-ድሩ ኮድ ንብረትነታቸው የሐበሻቪው አይፒቲቪ ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር እና/ወይም የፈቃድ ሰጪዎቹ ሲሆን አግባነብት ባላቸው የሃገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የቅጂ መብት ሕጎች የተጠበቁ ናቸው (የቅጂ መብት 2012/13 ሐበሻቪው፡ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው)፡፡ ከእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ውጪ በመካነ-ድሩ በሐበሻቪው አይፒቲቪ ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ላይ በግልጽ ካልተፈቀደ በስተቀር የመካነ-ድሩን ይዘትና የመካነ-ድሩን ኮድ መቅረጽ፣ በሙሉም ሆነ በከፊል መቅዳት፣ ማከፋፈል፣ ማተም፣ መከየን፣ መቀየር፣ ማውረድ፣ ማሰራጨት፣ ማስተላለፍ፣ መሸጥ፣ ፈቃድ መስጠት፣ ማባዛት፣ በመካነ-ድሩ ይዘትም ሆነ በመካነ-ድሩ ኮድ ላይ ተመስርቶ ሌሎች ሥራዎችን መፍጠር፣ ማከፋፈል፣ መለጠፍ፣ ለሕዝብ ማሳየት፣ ፍሬም ማድረግ፣ ማስተሳሰር ወይም በሌላ በማንኛውም መንገድ ያላግባብ መጠቀም አይፈቀም፡፡ ማንኛውም ለእርስዎ በግልጽ ያልተሠጠ መብት የተጠበቀ ነው፡፡ የትኛውም የቅጂ መብት ጥሰት ከባድ የፍትሐ-ብሔርና የወንጀል ቅጣቶችን ያስከትላል፡፡ ተላላፊዎች በሕጎቹ የተቀመጡትን የመጨረዎቹን ከባድ ቅጣቶች እንዲቀበሉ የሚያደርጉ የወንጀል ክሶች ይመሰረትባቸዋል፡፡

3. ምዝገባ

እያንዳንዱ ተጠቃሚ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ጋር መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ ተጠቃሚው በምዝገባው ወቅት የተወሰነ መረጃ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ ይህንን ካደረገ በኋላ የመጠቀሚያ አካውንት ከመጠቀሚያ ስምና ይለፍ ቃል ጋር ይሰጠዋል፡፡ ምዝገባው ተጠቃሚው አገልገሎቶቹን ሰብስክራይብ እንዲያደርግና የይዘቱን ውስን መብቶች እንዲገዛ ዕድል ይሰጣል፡፡ ተጠቃሚው በምዝገባ እና/ወይም፣ ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅት ትክክለኛ፣ ሙሉና ሕጋዊ የሆነ መረጃ ለመስጠት፤ የሚሰጠውን መረጃ ወቅታዊ ለማድረግና ለማዘመን ይስማማል፡፡ ተጠቃሚው ከዚህ በተጨማሪ የሚጠቀምበትን አካውንት ዝርዝና የይለፍ ቃል በምስጢር ለመያዝና ካልተፈቀደና አግባብነት ከሌለው ተጠቃሚ ለመጠበቅ ይስማማል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበርን ከመጠቀሚያ አካውንቱ ጋር የተያያዘ መረጃ መጥፋት ወይም ያላግባብ ጥቅም መዋልን በተመለከተ በተጠቃሚውም ሆነ በሌላ ሦስተኛ ወገን ተጠያቂ ሊደረግ እንደማይችል ተጠቃሚው ዕውቅና ይሰጣል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ማንኛውም ተጠቃሚ የሰጠው መረጃ ሀሰተኛ፣ የተሳሳተ ወይም የሚያሳስት ሆኖ ሲገኝ አገልግሎቱን የማቋረጥ መብት አለው፡፡ ተጠቃሚው፣ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ተጠቃሚው የሚሰጠውን መረጃ (ተጠቃሚው ከሚጠቀመው የክፍያ ዘዴ ጋር በተያያዘ የሚሰጠውን መረጃ ጨምሮ) የሚይዝ ሲሆን ይህንንም የሚያደርገው የተጠቃሚዎችን አካውንቶች ለማስተዳደርና የአገልግሎት ሒሳብን ለመጠየቅ ነው፡፡ ተጠቃሚውም ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የሰጠውን መረጃ እንዲይዝና እንዲጠቀምበት በይፋ ፈቃዱን ሰጥቷል፡፡

4. የመጠቀሚያ አካውንት

የመጠቀሚያ አካውንቱን ምስጢራዊነትና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት የተጠቃሚው ብቻ ነው፡፡ ተጠቃሚው የአካውንቱን መረጃ ለሌላ አካል አንዳይገልጽ ይመከራል፡፡ ተጠቃሚው አካውንቱን በመጠቀም ለሚደረጉ ማንኛውም ተግባራት በብቸኝነት ኃላፊነት የሚወስድ ሲሆን ያልተፈቀደለት አካል አካውንቱን ሲጠቀም ወይም የደኅንነት ጥሰት ሲኖር ወዲያውኑ ለሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ተጠቃሚው በማንኛውም ጊዜ በመግቢያው ድረ-ገጽ ላይ የሚገኘውን መመሪያ በመከተል የረሳውን የይለፍ ቃል መልሶ ማግኘት ወይም መቀየር ይችላል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር አካውንቱን ለመጠቀም ፈቃድ የሌለው ሰው በመጠቀሙ ለሚደርስ ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ተጠቃሚው ለሚገዛውና ለሚቀበለው ማንኛውም ዕቃ ኃላፊነት የሚወስደው ራሱ ሲሆን ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ተጠቃሚው በገዛው ዕቃ ላይ ለሚያጋጥም ማንኛውም ብልሽት፣ ውድመት ወይም ጉዳት ተጠያቂ አይሆንም፡፡

5. ሰብስክራይብ ስለማድረግ

5.1 አገልግሎታችንን ሰብስክራይብ ሲያደርጉ በንዑስ-አንቀጽ 5.5 የመደበኛ ክፍያ ደንቦች መሠረት በመደበኛነት በሚደረግ ክፍያ ለሚገኝ ሰብስክሪፕሽን አገልግሎት ስምምነት ለማድረግ ፈቃድዎን አንደሰጡ ይቆጠራል፡፡

5.2 ደኅንነቱ በተጠበቀው የክፍያ ሥርዓታችን በኩል የሚደረጉ ሰብስሪፕሽኖች የሚከወኑት ደኅንነቱ በተጠበቀው ሰብስክሪፕሽንና መደበኛ ክፍያዎች አገልግሎት በኩል ሲሆን በየጊዜው በራሳቸው የሚታደሱ ናቸው፡፡ ሰብስክራይብ አድራጊዎች የእድሳት ክፍያው ከመቆረጡ በፊት በተመዘገቡበት የኢሜይል አድራሻቸው በኩል ማስታወሻ ይደርሳቸዋል፡፡ መደበኛ ክፍያዎቹን በማንኛውም ጊዜ በአካውንትዎ በኩል ወይም በስልክ መሰረዝ ይችላሉ፡፡

5.3 ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ተጠቃሚው ላልተጠቀመበት የትኛውም አገልግሎት ገንዘብ ተመላስሽ አያደርግም፡፡ ሆኖም ሰብስከሪፐሽኑ እንዲቆም ማድረግ (በዚህ ሳይወሰንና ለአገልግሎቶች የሚደረግ ክፍያን ጨምሮ) ተጠቃሚው በዚህ ስምምነት መሠረት ያሉበትን ኃላፊነቶች ቀሪ አንዲሆን አያደርግም፡፡

በቅናሽ ዋጋ ለደንበኞች የቀረቡ በመሆናቸው የሩብ ዓመት፣ የመንፈቅ ዓመትና የዓመታዊ ጥቅሎችን ክፍያ መሠረዝ አይቻልም፡፡ በልዩ ሁኔታ መደበኛ ያልሆነ ሰብስክሪፕሽን በሚሰረዝበት ጊዜ ተመላሽ የሚደረግ ገንዘብ (ተመላሽ ሊደረግ ከተወሰነ) የሚሰላው አግባብነት ባለው ጥቅል ወርሃዊ ክፍያ መሠረት ይሆናል፡፡

የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር አስተዳደር መደበኛ ያልሆነ ሰብስክሪፕሽን ስረዛን በተመለከተ የሚያሳልፈው ውሳኔ ይግባኝ የሌለው ይሆናል፡፡

5.4 ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የቲቪ ቦክስ ጥቅሎች

ደንበኛው ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር አገልግሎቶቹን ለማስተዋወቅና ተጨማሪ ደንበኞችን ለመሳብ አገልግሎቶቹን ለማቅረብ አስፈላጊ ግብዓት የሆነውን የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ቲቪ ቦክስ በመያዣ መርኃ-ግብር በቅናሽ ዋጋ እያቀረበ እንደሆነ ይረዳል፤ ዕውቅናም ይሠጣል፡፡ ደንበኛው አገልግሎቱን መጠቀም ሲያቆም ወይም ሲሠርዝ የኩባንያው ሥራ በእጅጉ ስለሚጎዳ እና ከባድ ኪሳራዎች ስለሚያጋጥሙት ቢያንስ አንድ (1) ዓመት ለሚሆን ጊዜ (ውል መሠረዝ የማይቻልበት ወቅት) የአገልግሎት ለውጥ/ሥረዛ ማድረግ የማይቻል ሲሆን ደንበኛው በኩባንያው የአገልግሎት ሥረዛ ፖሊሲ መሠረት የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የቲቪ ቦክስ ለደንበኛው በደረሰውና የምርት ችግር እንዳለበት በታወቀ በ14 ቀናት ውስጥ መመለስ ይኖርበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ውል መሠረዝ በማይቻልበት ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ደንበኛው አገልግሎቱን ማግኘት ለማቆም በሚወስንበት ጊዜ የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ደንበኛው የ 6 ወራት የሰብስክሪፕሽን ክፍያ የሚሆን ገንዘብ አገልግሎቱን ሲያስጀመር ወይም የመጀመሪያውን ሰብስክሪፕሽን ሲደርግ ከተጠቀመው የክፍያ ሥርዓት ላይ ተቀናሽ የማድረግ መብት አለው ወይም ደንበኛው በአግባቡ የሚሠራን የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የቲቪ ቦክስ በትክክለኛው ማሸጊያ የመመለስ ኃላፊነት/ግዴታ ይኖርበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደንበኛው በአግባቡ የሚሰራን የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የቲቪ ቦክስ በትክክለኛው ማሸጊያ በማድረግ የማይመልስ ከሆነ ኩባንያው የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የቲቪ ቦክስ
ወጪ ደንበኛውን የማስከፈል መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

5.5 የመደበኛ ክፍያ ደንቦች

5.5.1 መደበኛ ክፍያዎች የሚከፈሉበት ጊዜ፡- ሰብስክሪፕሽንዎ ከሚጠናቀቅበት ቀን አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በመካነ-ድራችን፣ በኢሜይል ወይም በሽያጭ ሠራተኞቻችን በኩል በተገለጸልዎት ወሰን ውስጥ በመደበኛነት የሚደረግ ክፍያ በሥርዓታችን አማካይነት ተቆራጭ ይደረጋል፡፡ የዕድሳት ዝርዝርና የክፍያውን መጠን የሚገልጽ የቅድመ-ክፍያ የማረጋገጫ ኢሜይል ይደርስዎታል፡፡

5.5.2 በሥርዓታችን አማካይነት የሚደረገው መደበኛ ተቆራጭ በማይሳካበት ውቅት በኢሜይል አድራሻዎ መልዕክት በመላክ ወይም በስልክ እናገኝዎታለን፡፡ በአንድ የክፍያ አማራጭ በኩል የሚደረግ መደበኛ ተቆራጭ በተደጋጋሚ በማይሳካበት ወቅት ይህንን የክፍያ አማራጭ በቋሚነት የመሰረዝ መብት ይኖረናል፡፡ ያስታውሱ፡- በክፍያ ሥርዓታችን አማካይነት በራሱ ተቆራጭ የሚደረገው መደበኛ ክፍያ ካልተሳካ አካውንትዎን ሌላ በቂ ስንቅ ባለው የክፍያ አማራጭ መተካት ይኖርብዎታል፡፡ ከሒሳብዎ ተቆራጭ ተደርጎ ክፍያ መፈጸም በሚኖርብዎት ጊዜ ካልከፈሉ የሚያገኙት አገልግሎት ሊታገድ ወይም በቋሚነት ሊሠረዝ ይችላል፡፡

5.5.3 የመደበኛ ክፍያ ሥረዛ፡- በየትኛውም ጊዜ መደበኛ ክፍያ ተቆራጭ እንዲደረግ የሠጡትን ፈቃድ መሠረዝ ይችላሉ፡፡ መደበኛ ክፍያውን [email protected] ላይ ኢሜይል መላክ ወይም በ + 251 944307017
ላይ የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን በማናገር መሰረዝ ይችላሉ፡፡ መደበኛ ክፍያው እንዲሰረዝ ያቀረቡት ጥያቄ እስኪስተናገድ እስከ 24 ሰአታት ሊፈጅ ይችላል፡፡ የወሩ ክፍያ ተቀናሽ እንዳይደረግብዎ ከፈለጉ የ 30 ቀኑ ጊዜ ከማለቁ በፊት መሰረዝ ይኖርብዎታል፡፡ ሰብስክሪፕሽንዎን ለመሠረዝ ጥያቄ ሲያቀርቡ ለሰብስክሪፕሽን ያደረጓቸው ክፍያዎች ተመላሽ አይደረጉም፡፡ በዚህ ፈንታ አሁን የሚገለገሉበት ሰብስክሪፕሽን እስከ መደበኛው የክፍያ ወቅት ቀጥሎ ከዚያ በኋላ
አገልግሎት መስጠት የሚያቆምና የመገልገያ ፈቃድዎ የሚሰረዝ ይሆናል፡፡ የአገልግሎት ሥረዛዎ ይፋዊ የሚሆነው ከኩባንያው የማረጋገጫ ኢሜይል ሲደርስዎ ብቻ ነው፡፡ ጥያቄው በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ በ + 251 944307017 ላይ በመደወል ሥረዛዎን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል፡፡

5.5.4 የመደበኛ ክፍያ መንገድ ለውጥ፡- በክፍያ ሥርዓታችን አማካይነት ክፍያ ተቆራጭ የሚደረግበትን መንገድ ለመለወጥ (ለምሳሌ፡- ከአንድ መጀመሪያ ጥቅም ላይ ሲውል ከነበረ የዴቢት ወይም ክሬዲት ካርድ ወይም የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ) ለመለወጥ ከፈለጉ በአዲሱ የክሬዲት ወይም የዴቢት ካርድ የሚደረግ ክፍያ የደንበኞች አገልግሎት ጋር በመደወል እንዲፈቀድ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡ ከዚህ በፊት ጸድቆ ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው የክፍያ መንገድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ይሰረዛል፡፡

6. ክፍያ

ተጠቃሚው፣ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ የሚቀበልበትን ሕጋዊ የክሬዲት ካርድ ያቀርባል፡፡ ተጠቃሚው በዚህ ስምምነት መሠረት ለሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በክሬዲት ካርዱ ለአገልግሎቱ ግዢዎችና ሌሎች ዝውውሮች ክፍያ የመጠየቅ፣ ተቀናሽ የማድረግና የመሰብሰብ ሥልጣን ይሰጣል፡፡

ተጠቃሚው ሁሉም አገልግሎቶችና ሰብስክሪፕሽኖች የክፍያ ጊዜያቸው ሲደርስ ለመክፈል ይስማማል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በክሬዲት ካርዱ በኩል ሌሎች ክፍያዎችን ወይም ግዢዎችን ወይም ከመጠቀሚያ አካውንቱና አገልግሎቶቹን ከመጠቀም ጋር በተገናኘ የተጠራቀሙ ተጨማሪ ክፍያዎችን (አግባብነት ሲኖራቸው ግብርና የዘገዩ ክፍያዎችና ቅጣት) ሊጠይቅና ተቀናሽ ሊያደርግ ይችላል፡፡

የተጠቃሚዎች አገልግሎቶቹን መጠቀም በኤሌክትሮኒክ መንገድ ስምምነቶችንና ግዢዎችን መፈጸምን ያካትታል፡፡ ተጠቃሚው ማናቸውምና ሁሉም በኤሌክትሮኒክ መንገድ የሚፈጽማቸው ስምምነቶችና ግዢዎች አስገዳጅ መሆናቸውን፣ ተጠቃሚው በዚህ ሰምምነት ደንቦች ለመገዛት መፍቀዱንና በዚህ ስምምነት ደንቦች መሠረት ለአገልግሎት ግዢዎች የሚደረግና ክፍያና ተቀናሽን እንዲሁም በዚህ ስምምነት መሠረት መከፈል ያለባቸውን ክፍያዎች ጨምሮ በክፍያ አስፈላጊ ሁኔታዎች ለመገዛት መስማማቱን የሚያሳዩ ስለመሆናቸው በግልጽ ዕውቅና በመስጠት ይስማማል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተጠቃሚው የስረዛ/መቋረጥ ማሳወቂያዎች፣ ፖሊሲዎች፣ ውሎች እና ማመልከቻዎችን ጨምሮ ከሁሉም ዝውውሮች ጋር የተያያዙ ቅጂዎች በኤሌክትሮኒክ መንገድ በሚሰጣቸው መረጃዎች ተገዢ ይሆናል፡፡ ተጠቃሚው በማንኛውም ጊዜ ለ [email protected] ኢሜይል በመላክ አገልግሎት ስለገዛባቸው ዝውውሮች መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡ ሆኖም ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለማንኛውም ተጠቃሚ የየትኛውንም መረጃ የወረቀት ቅጂዎችን አይልክም፡፡

7. ሥርጭት

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ይዘቱ ለተጠቃሚው አንዲደርስ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል፡፡ ተጠቃሚው ከሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ቁጥጥር ውጪ በሆኑ እንደ ከባድ ነፋስና ዝናብ፣ እሳት፣ ሕይወት የጠፋበት አደጋ፣ ያልተጠበቀ የሥራ ማቆም፣ የኃይል መቋረጥ፣ የሳተላይት ብልሽት፣ አድማ፣ የአሠሪ ክልከላ፣ የአሠሪና ሠራተኛ ክርክር፣ ሕዝባዊ ሁከት፣ ዐመጽ፣ ጦርነት፣ አገራዊ የአስቸኳይ ጊዜ፣ የመንግስት ድርጊት፣ የሕዝብ ጠላት ድርጊት ወይም ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተመሳሳይነት የሌለው ምክንያት ያሉ ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች የተነሳ ይዘቱን ለተጠቃሚው ማድረስ ላይችል እንደሚችል ይገነዘባል፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች ለሚቋረጥ ወይም ለሚዘገይ ሥርጭት ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ኃላፊ እንደማይሆን ይስማማል፡፡

አንዳንድ ጊዜ በቴክኒክ ችግሮች ምክንያት ተጠቃሚው የጠየቃቸው ምርቶች ወይም አገልግሎቶችን ማድረስ የማይቻል ይሆናል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በራሱ ብቸኛ ምርጫና መብት ዕቃውን ወይም
አገልግሎቱን ሊተካ ወይም ተገቢ በሆነ ጊዜ ውስጥ ሊደርስ ያልቻለው ዕቃ ወይም አገልግሎት የተገዛበትን ገንዘብ ተመላሽ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ተጠቃሚው አገልገሎቶቹን በሚጠቀምበት ወቅት የሚያስከፋ፣ አስጸያፊና ቅቡልነት የሌለው ይዘት
ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ተጠቃሚው በአገልግሎቶቹ የሚጠቀመው በራሱ ብቸኛ ኃላፊነት እንደሆነና ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ተጠቃሚው ለሚያጋጥመው ማንኛውም የሚያስከፋ፣ አስጸያፊና ቅቡልነት የሌለው ይዘት ኃላፊ እንደማይሆን ይስማማል፡፡

ተጠቃሚው፣ አንዳንድ የአገልግሎቱ ገጽታዎች የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበርን ቀጣይነት ያለው ሥራ እንደሚፈልጉ፤ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የአገልግሎቶች ለውጥ በሚያደርግበት ወቅት መቆራረጥና መቋረጥ ሊኖር እንደሚችል፣ ተጠቃሚው ከለውጡ ወይም ከመቋረጡ በፊት ሲያገኛቸው የነበሩ አገልግሎቶችን ላያገኝ እንደሚችልና ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለዚህ ኃላፊነት አንደማይወስድ ይገነዘባል፡፡

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በየትኛውም ጊዜ ያለምንም ማሳወቂያ ማንኛውንም አገልግሎትና ይዘት የመለወጥ፣ የማገድ፣ የማስወገድ፣ ወይም አገልግሎት እንዳይሰጡ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በየትኛውም ሁኔታ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በዚህ ስምምነት መሠረት አገልግሎቶች፣ ይዘቶችና መገልገያዎችን በማስወገዱና ወይም አገልግሎት እንዳይሰጡ በማድረጉ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በማናቸውም ምክንያትና ያለምንም ማሳወቂያ አንዳንድ የአገልግሎት ገጽታዎችና ክፍሎች ላይ ገደብ ሊያኖር የሚችል ሲሆን ይህንን በማድረጉም ተጠያቂ አይሆንም፡፡

8. ገደቦች

ተጠቃሚው፣ በአገልግሎቶቹ በኩል የተገዙት ምርትና አገልግሎቶች ደጂታል መረጃውን የሚጠብቅና በሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር እና በፈቃድ ሰጪዎቹ በተደነገጉ የአጠቃቀም ሕግጋት መሠረት የምርቶችና አገልግሎቶቹ አጠቃቀም ላይ ወሰን የሚያደርግ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የደኅንነት መከላከያ ማዕቀፍ የተካተተባቸው አንደሆነ ይገነዘባል፡፡ ተጠቃሚው ምርቶችና አገልግሎቶቹን ለራሱና ለንግድ ባልሆነ መንገድ ብቻ ለመጠቀም ፈቃድ ተሰጥቶታል፡፡ ተጠቃሚው ራሱም ሆነ ሌላ ሰው የደኅንነት ማዕቀፉን እንዲጥስ፣ በቅልብስ-ምህንድስና እንዲያዋቅር፣ ኮዱን አንዲያፍታታ፣ ምርቶችን እንዲበታትን ወይም በሌላ በማንኛውም መልኩ ከአጠቃቀም ሕግጋቱ ጋር የተገናኙ የደኅነነት መጠበቂያዎችን በማንኛውም ምክንያት አላግባብ እንዲነካካ ማድረግ ወይም መሞከር የተከለከለ ነው፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የአጠቃቀም ሕግጋቱ መተግበራቸውን ለማረጋገጥ ቁጥጥርና ክትትል ሊያደርግ የሚችል ሲሆን የአጠቃቀም ሕግጋቱን በማሳወቂያም ሆነ ያለማሳወቂያ የማስከበር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ማበረታቻዎች

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በተወሰነ ጊዜ አንዳንድ ማበረታቻዎችን ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ከማበረታቻዎቹ ተጠቃሚ መሆን መቻል የሚወሰነው በሚቀርቡት ማስተዋወቂያዎች ዝርዝር መስፈርት መሠረት ይሆናል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የትኛውም ጊዜ የሚያቀርባቸውን ማስተዋወቂያዎች በራሱ ውሳኔ የመለወጥ ወይም የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በመካነ-ድሩ አገልግሎት ለማግኘት ግዢ ያከናወነ ተጠቃሚ በማበረታቻዎች እየተጠቀመ ሳለ የአገልግሎቱ ዘመን ከማብቃቱ በፊት አገልግሎቱን ቢሰርዝ የተጠቀመበትን የማበረታቻ ዋጋ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

10. ሊሟሉ የሚገባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች

አገልግሎቱን በመጠቀም ፊልሞችን፣ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን/የድምጽ ወይም የቴሌቪዥን ፕሮግራችን ለማግኘት የሚጣጣም መሣሪያ፣ የኢንተርኔት አቅርቦትና አንዳንድ ሶፍትዌሮች የሚያስፈልጉ ሲሆን በተወሰነ ጊዜ ማዘመንና ማሻሻያዎችን ማግኘት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ተጠቃሚው አገልግሎቶቹን ማግኘት መቻሉ በእነዚህ ሁኔታዎች ሊወሰን ይችላል፡፡ አገልግሎቱን ለማግኘት ፈጣን የኢንተርኔት አቅርቦት (ቢያንስ 2 ሜጋቢትስ በሰከንድ ፍጥነት ያለው) ብሮድባንድ ኢንተርኔት ያስፈልጋል፡፡

11. የግላዊነት ፖሊሲ

11.1 ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የተጠቃሚዎቹን የግላዊነት መብት ያከብራል፡፡ በቅድሚያ ፈቃድዎን ሳያገኝ ለሌላ ሦሰተኛ ወገን መረጃዎን አያጋራም፣ አይሸጥም ወይም በሌላ መንገድ አያከፋፍልም፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የደንበኞቹን ጥያቄዎች በፍጥነት ለማስተናገድ ሲል የግል መረጃ ሊጠይቅዎ ይችላል፡፡ ስምዎን፣ አድራሻዎን፣ የስልክ ቁጥርዎን እና የኢሚይል አድራሻዎን ጨምሮ ለሃበሻቪው የሚሰጡት ማንኛውም መረጃ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በውስጥ አሠራር የአባልነት ጥያቄዎን ለማስተናገድና አመርቂ የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ብቻ የሚጠቀምበት ይሆናል፡፡

11.2 ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለየትኛውም ሦስተኛ ወገን በግል የሚለዩበትንም ሆነ ጥቅል መረጃዎን አይሸጥም፣ አይለውጥም ወይም አያከራይም፡፡ ስምዎና ሌሎች የግል መረጃዎችዎ ከእርስዎ ጋር የመልእክት ልውውጥ ለማድረግ ብቻ የምንጠቀምባቸው ናቸው፡፡

11.3 ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የተጠቃሚዎቹን የኢሜይል አድራሻ የሚሰበስብ ሲሆን የማስተዋወቂያ የኢሜይል መልእክቶችን ለሁሉም የተመዘገቡ ተጠቃሚዎቹ የመላክ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጠቃሚዎች እንዲህ ዓይነት የኢሜይል መልእክቶች እንዲደርሳቸው ካልፈለጉ በመካነ-ድሩ ቅንብር በኩል ማስተካከያ ማድረግ ይችላሉ፡፡

11.4 ገንዘብ-ነክ መረጃ የሚሰበሰበው ተጠቃሚዎች ለምዝገባ ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥና ለተጠቀሙባቸው ምርቶችና አገልግሎቶች ክፍያ ለመጠየቅ ብቻ ነው፡፡

11.5 በሰርቨራችን የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመመርመር፣ መካነ-ድሩን ለማስተዳደርና ተጠቃሚዎች በመካነ-ድሩ የሚያደርጉትን ግብይት ለመከታተል የተጠቃሚዎችን የአይፒ አድራሻ እንጠቀማለን፡፡

11.6 በመካነ-ድራችን የሚያደርጉትን ግብይት ይዘት እና/ወይም የሪፈራል መረጃ ለመከታተል ኩኪዎችን እንጠቀማለን፡፡ “ኩኪዎች” ኢንተርኔት የሚጠቀሙበት መተግበሪያ በኮምፒውተርዎ የማስታወሻ ክፍል የሚያስቀምጣቸው ጥቃቅን
መረጃዎች ናቸው፡፡ ኩኪዎችን የምንጠቀመው እርስዎ መካነ-ድራችንን በቀላሉ እንዲጠቀሙ ለማስቻልና የምናቀርባቸውን አገልግሎቶች ጥራት ለማሻሻል የሚረዱንን አንዳንድ ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን ለመከታተል ነው፡፡ በአብዛኛዎቹ የኢንተርኔት መጠቀሚያ መተግበሪያዎች ኩኪ ሲቀበሉ እንዲያሳውቅዎ ማድረግ ወይም ኩኪዎችን ማገድ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ኩኪዎችን ሲሰርዙ ወይም ሲያግዱ አንዳንድ የመካነ-ድሩን ክፍሎች ለመጠቀም የመጀመሪያውን የተጠቃሚ መለያና የይለፍ ቃል በድጋሚ ማስገባት አንደሚኖርብዎ እባክዎ ልብ ይበሉ፡፡

11.7 የግል መረጃዎን ለሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለመስጠትም ሆነ ላለመስጠት መወሰን ይችላሉ፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በመካነ-ድሩ ስለሚሰበስበው የግል መረጃ የሚያቀርበው ማሳወቂያ ይህንን ውሳኔ ለመወሰን ያግዝዎታል፡፡ የግል መረጃዎን ላለመስጠት ከወሰኑ የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር መካነ-ድር በከፊል መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን ከእርስዎ ጋር የመረጃ ልውውጥ እንድናደርግ የሚጠይቁ አንዳንድ አማራጮችን፣ አቅራቦቶችንና አገልግሎቶችን ማግኘት የማይችሉ ይሆናል፡፡

11.8 ይሀንን መካነ-ድር በመጠቀምዎ በግላዊነት ፖሊሲያችን ደንቦችና ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ከላይ ለተቀመጠው ዓላማ ሲል የግል መረጃዎትን እንዲሰበስብ ፈቃድዎን እንደሰጡ ይቆጠራል፡፡ የግላዊነት ፖሊሲያችን ላይ ለውጥ ካደረግን የለውጦቹን ዝርዝር በተቻለን ፍጥነት በመካነ-ድሩ ላይ አግባብነት ላለው የጊዜ ቆይታ በመለጠፍ እንዲደርስዎ የምናደርግ ይሆናል፡፡

12. የደኅንነት ፖሊሲ

ይህ መካነ-ድር በእኛ ቁጥጥር ሥር ያለ መረጃ እንዳይጠፋ፣ ያላግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውልና እንዳይቀየር የሚከላከል የደኅንነት ሥርዓት ያለው ነው፡፡ ወደ መካነ-ድራችን እየመጣ ያለ እና ከመካነ-ድራችን እየወጣ ያለ መረጃ የኤስኤስኤል ኢንክሪፕሽን ፕሮቶኮሎችን በመጠቀም የተመሰጠረ ነው፡፡ ሁሉንም የተጠቃሚዎች መረጃ የምናስቀምጠው የተደራሽነት ቁጥጥር በሚደረግባቸውና ጥንቃቄ የሚያሻቸው መረጃዎች በሚመሰጠሩባቸው ደኅነነታቸው በተጠበቁ የመረጃ ቋቶች ውስጥ ነው፡፡ ይህ መረጃ ጥቅም ላይ የሚውለው በዚህ የግላዊነት መግለጫው ለተዘረዘሩት ዓላማዎች ብቻ ነው፡፡ ደኅንነቱ የተጠበቀው የሰርቨር ሶፍትዌራችን ዘርፉ በደረሰበት የኤሌክትሮኒክ ግብይት የደኅንነት መጠበቂያዎች የተጠበቀ ነው፡፡ ስምዎን፣ አድራሻዎንና የክሬዲት ካርድ ቁጥርዎን ጨምሮ ሁሉንም የግል መረጃዎን በማመስጠር መረጃዎ በኢንተርኔት ሲንቀሳቀስ ማንም እንዳይደርስበት በብቃት ይከላከላል፡፡ ሁሉም የደንበኞቻችን ክሬዲት ካርዶች በመረጃ ቋታችን ውስጥ ተመስጥረው ይቀመጣሉ፡፡

13. የሦስተኛ ወገኖች ይዘቶችና መካነ-ድሮች

ተጠቃሚው በአገልግሎቶቹ በኩል የሚያገኛቸው አንዳንድ ይዘቶች፣ ምርቶችና አገልግሎቶች የሦስተኛ ወገኖችን ይዘቶች ሊያካትት እንደሚችል ይገነዘባል፡፡ በተጨማሪም ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የአንዳንድ የሦስተኛ ወገን መካነ-ድሮችን ማስፈንጠሪያዎች ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ተጠቃሚው ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የሦስተኛ ወገኖችን ይዘት ወይም መካነ-ድር የመመርመር፣ የመመዘንም ሆነ ትክክለኛነታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንደሌለበት በመገንዘብ ይስማማል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሦስተኛ ወገኖች ይዘት፣ መካነ-ድሮች፣ ሌሎች ይዘቶች፣ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ምንም አይነት ዋስትና ወይም ማረጋገጫ አይሰጥም፣ ስለ እነርሱም በምንም ዓይነት ሁኔታ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

14. ተፈጻሚነት

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ይህን ስምምነት ለማስፈጸም እና ወይም ተፈጻሚነቱን ለማስከበር አስፈላጊና አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች (ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ከተጠቃሚዎች የአገልግሎችና እና/ወይም ምርቶች አጠቃቀም ጋር በተገናኘ ከሚደረግ ከማንኛውም የሕግ ሒደት ጋር የመተባበር እና/ወይም የተጠቃሚው የአገልግሎቶች እና/ወይም የምርቶች አጠቃቀም “ሕገ-ወጥ ነው” እና/ወይም “መብቴን የሚጥስ ነው” ከሚል ሦስተኛ ወገን ጋር የመተባበርን ጨምሮ እና ሌሎችንም) የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጠቃሚው፣ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር አግባብነት ያለው ወይም አስፈላጊ እንደሆነ ሲያምን ለሕግ አካላት፣ ለመንግስት ባለሥልጣናት፣ እና/ወይም ሦስተኛ ወገን የምዝገባ እና/ወይም የአካውንት መረጃ የመስጠት መብት እንዳለው የሚገነዘብ ሲሆን በዚህም ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበርን ኃላፊ ላለማድረግ ይስማማል፡፡

15. ለአካለ-መጠን ያልደረሰ ተጠቃሚ

አንድ ለአካለ-መጠን ያደረሰ ተጠቃሚ የዚህን ስምምነት ደንቦችና ሁኔታዎች በደንብ መረዳቱን ለማረጋገጥ ከወላጅ/አሳዳጊ ጋር ደንቦቹን ማጤን ይኖርበታል፡፡ አገልግሎቱን ለመግዛት ለክፍያው ኃላፊነት የሚወስድና ተጠያቂ የሚሆን የተፈቀደለት የክሬዲት ካርድ ያዥ (ወላጅ/አሳዳጊ) ያስፈልጋል፡፡

16. የንብረት መብቶች

ተጠቃሚው ግራፊክስ፣ ድምጽ፣ የፊልም ቅንጭቦችና የአርታኢ ይዘቶችን ጨምሮ ሌሎችም ንብረትነታቸው የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር እና/ወይም የፈቃድ ሰጪዎቹ የሆኑ የንግድ ምስጢሮችንና ይዘቶችን
እንደያዙና የቅጂና የንግድ ምልክትንና ሌሎች የንብረት መብቶችን ጨምሮ አግባብነት ባላቸው የአእምሮአዊ ንብረት መብቶችና ሌሎች ሕጎች የተጠበቁ መሆናችውን በመገንዘብ ይስማማል፡፡ ተጠቃሚው እነዚህን የንግድ ምስጢሮችና ይዘቶች
ይህንን ስምምነት ባከበረ መልኩ አገልግሎቶቹን ለመጠቀም ካልሆነ በስተቀር በሌላ በማንኛውም መንገድ መጠቀም አልተፈቀደለትም፡፡ የትኛውንም የአገልግሎቶቹን ክፍል በየትኛውም መንገድና መልክ ማባዛት አይፈቀድም፡፡

ተጠቃሚው አገልግሎቶቹን በምንም ዓይነት መልኩ ላለመቀየር፣ ላለማከራየት፣ ላለማበደር፣ ላለመሸጥ፣ ላለማከፋፈል ወይም በአገልግሎቶቹ በመመስረት ሌሎች ሥራዎችን ላለመፍጠር እና የግንኙነት መረቡን ጥሶ መግባትና ማጨናነቅን ጨምሮ በሌላም ባልተፈቀደለት በየትኛውም መንገድ አገልግሎቶቹን ላለመጠቀም ይስማማል፡፡

የይዘቶችን ጥንቅር፣ ልጠፋዎችን፣ የሌሎች የኢንተርነት አገልግሎቶች ማስፈንጠሪያወችን እና የእነዚህ አገልግሎቶች መግለጫዎችን ጨምሮ የምስል-ድምጽ ቅንጭቦችን፣ ፊልሞችን፣ ግራፊክሶችን፣ ምስሎችን፣ አኒሜሽኖችን፣ ስእሎችን፣ የአርታኢ ይዘቶችንና ሶፍትዌርንና የሁሉም የአገልግሎቶችና ምርቶቹን ጨምሮና ሌሎች የቅጂ መብቶች ባለቤት ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር እና/ወይም ፈቃድ ሰጪዎቹ ናቸው፡፡ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ንብረቶች
በሌላ ኤሌክትሮኒክ ሆነ የሕትመት ሚድያ ማባዛት የተከለከለ ነው፡፡ ሶፍትዌሩንም ሆነ የትኛውንም የአገልግሎቱን ክፍል በዚህ ስምምነት ከተፈቀደው ውጪ መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር እና/ወይም የፈቃድ ሰጪዎቹን የአእምሮአዊ ንብረት መብት የሚጥስ ነው፡፡ የእነዚህ የቅጂ መብቶች ጥሰት ተጠቃሚውን የገንዘብ ካሳን ጨምሮ ለፍትሐ-ብሔርና ለወንጀል ቅጣቶች የሚዳርግ ነው፡፡

ሐበሻቪው፣ የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር አርማ እና ሌሎች የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የንግድ ምክቶች፣ የአገልግሎት ምልክቶች፣ ግራፊክስ እና ከአገልግሎቶቹ ጋር በተገናኘ
ጥቅም ላይ የሚውሉ አርማዎች የሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የንግድ ምልክቶችና የተመዘገቡ የንግድ ምልክቶች ናቸው፡፡ ተጠቃሚው የተጠቀሱትን የንግድ ምልክቶች የመጠቀምም ሆነ ሌላ መብትም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡

17. ማሳሰቢያ

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ተጠቃሚዎች የሚያገኙት አገልግሎት የማይቆራረጥና እንከን- አልባ እንደሆነ አድርጎ አያቀርብም፣ ዋስትናም አይሰጥም፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር
በተለያዩ ጊዜያት ተጠቃሚውን አሳውቆም ሆነ ሳያሳውቅ አገልግሎቶቹን ላልተወሰነ ጊዜ ሊያግድ፣ ሊያስወግድ ወይም በማንኛውም ጊዜ አገልግሎቶቹን ሊሰርዝ ወይም ሊያቋርጥ እንደሚችል ተጠቃሚው ይስማማል፡፡

ተጠቃሚው አገልግሎቶቹን የመጠቀምም ሆነ ለመጠቀም ያለመቻል የራሱ ኃላፊነት ብቻ እንደሆነ ይስማማል፡፡ አገልግሎቶቹና በአገልግሎቶቹ በኩል ለተጠቃሚው የሚደርሱ ምርቶችና አገልግሎቶች ተዘዋዋሪ የገበያ ብቁነት ዋስትናን፣ ለአንድ ዓላማ መዋል የመቻል ብቁነትን፣ ባለቤትነትንና፣ የሕግ ጥሰትን ጨምሮ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተገለጸ ምንም ዓይነት ዋስትና የሌላቸውና እንደሆኑትና አንዳሉት የሚቀርቡ ናቸው፡፡

ከመገኛዎት አንጻር ከፈቃድና ሌሎች ትክክለኛ ምክንያቶች የተነሳ አንዳንድ የሥርጭት ቀጣናዎችን ከማገድ ጋር በተገናኘ አንዳንድ ጣቢያዎችን ላያገኙ ይችላሉ፡፡

18. ኃላፊነት

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር፣ አስተዳዳሩ፣ መኮንኖቹ፣ ሠራተኞቹ፣ ተባባሪዎቹ፣ ወኪሎቹ፣ ቅጥር ያልሆኑ ሠራተኞቹ ወይም ፈቃድ ሰጪዎቹ በየትኛውም ጊዜና በማኝኛውም ሁኔታ ተጠቃሚዎች የትኛውንም
አገልግሎቶች ሲጠቀሙ ለሚያጋጥሙ ቀጥተኛ፣ ተዘዋዋሪ፣ በስምምነቱ ጥሰት ምክንያት ለሚከሰቱ የቅጣት፣ ልዩ ወይም ተከታይ ጉዳቶች ወይም ስህተቶች ወይም የተዘለሉ ይዘቶች፣ ወይም የተለጠፉትን፣ የተሠራጩትን ወይም በሌላ መንገድ
በአገልግሎቶቹ በኩል የቀረቡትን ይዘቶች ወይም ምርቶች በመጠቀም የደረሰ ማንኛውም ኪሳራ ወይም ጉዳትን (ሊፈጠሩ እንደሚችሉ መረጃው ቢኖረውም እንኳ) ጨምሮና ሌሎች አገልግሎቶቹን ከመጠቀም ጋር በተገናኘ ለሚነሱ ጥያቄዎች ኃላፊ አይሆኑም፡፡ ተከታይ ወይም በስምምነቱ ጥሰት ምክንያት ለሚከሰቱ ጉዳቶች ኃላፊነት በውል እንዲቀር ወይም እንዲወሰን በማይፈቅዱ ሃገራት ወይም የሕግ ሥርዓቶች ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የሚኖርበት ኃላፊነት በሕግ የሚፈቀደውን ያህል ብቻ ይሆናል፡፡

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ተጠቃሚው አገልግሎቶቹን ለመጠቀም የሚሰጠውን መረጃ ለመጠበቅ አግባብነት ያለውን ጥረት ያደርጋል፡፡ ሆኖም ተጠቃሚው መረጃ የሚሰጠው በራሱ ኃላፊነት እንደሆነና
ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ተጠቃሚው ከሰጠው መረጃ ጋር በተያያዘ ለሚያጋጥመው ማንኛውም ጉዳት ወይም ኃላፊነት ተጠያቂ እንደማይሆን ተጠቃሚው በመገንዘብ ይስማማል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና
መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር አገልግሎቶቹ ከመጥፋት፣ ከብልሽት፣ ከጥቃት፣ ከቫይረሶች፣ ከመቋረጥ፣ ሃክ ከመደረግና ሌሎች የሳይበር ደኅንነት ጥሰቶች ነጻ ስለመሆናቸው ዋስትና የማይሰጥ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ለሚነሳ ጥያቄ ኃላፊ
አይሆንም፡፡ ተጠቃሚው የሚጠቀምበትን የኮምፒውተር ሥርዓት ሌላ ቅጂ የማስቀመጥ ኃላፊነት የራሱ ብቻ ይሆናል፡፡

19. ማስቀረትና ካሣ

ተጠቃሚው አገልግሎቶቹን በመጠቀም ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበርን፣ አስተዳዳሩን፣ መኮንኖቹን፣ ሠራተኞቹን፣ ተባባሪዎቹን፣ ወኪሎቹን፣ ቅጥር ያልሆኑ ሠራተኞቹን እና ፈቃድ ሰጪዎቹን ተጠቃሚው ይህን ስምምነት ከማፍረሱ፣ አገልግሎቶቹን ከመጠቀሙ ጋር በተያያዘ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ወይም ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ይህ ስምምነት መጣሱን በመጠርጠር በሚያደርገው ምርመራ በሚወስዳቸው እርምጃዎች ወይም በእንደዚህ ዓይነት ምርመራ በእርግጥም ጥሰት ስለመፈጸሙ በሚያገኛቸው ግኝቶች ኃላፊ ላለማድረግና ካሣ ለመክፈል ይስማማል፡፡ ተጠቃሚው ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር፣ አስተዳዳሩ፣ መኮንኖቹ፣ ሠራተኞቹ፣ ተባባሪዎቹ፣ ወኪሎቹ፣ ቅጥር ያልሆኑ ሠራተኞቹ እና ፈቃድ ሰጪዎቹን ላይ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃን ወይም ይዘትን ለማስተናገድ ፈቃደኛ ያለመሆንና የማስወገድን ውሳኔን ተከትሎ ወይም ይህ ስምምነት ስለመጣሱ ጥርጣሬ ኖሮ ከሚያደርገው ምርመራ ወይም ይህ ስምምነት ስለመጣሱ ድምዳሜ ላይ ከመድረሱ የተነሳ ለሚደርስ ጉዳት ክስ መመስረትና ከእነርሱ የጉዳት ካሣ መጠየቅ አይችልም፡፡ ይህ የማስቀረትና የካሣ አንቀጽ በዚህ ስምምነት በግልጽ በተቀመጡም ሆነ ከስምምነቱ መንፈስ እንደተቀመጡ በሚቆጠሩ ጥሰቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

20. ስለ መቋረጥ

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃየተ/የግል ማኅበር፣ ተጠቃሚው ይህን ስምምነት ሲጥስ ወይም ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃየተ/የግል ማኅበር መከፈል ያለባቸውን ክፍያዎችን ለመክፈል አለመቻልን፣ ለሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃየተ/የግል ማኅበር ሕጋዊ የክሬዲት ካርድ አለማቅረብን ወይም ትክክለኛና የተሟላ የምዝገባ መረጃ አለመስጠትን፣ የአካውንት መረጃን መጠበቅ አለመቻልን ወይም የአጠቃቀም ሕግጋቱን ወይም የሶፍትዌሩን ፈቃድ
መጣስን ጨምሮና በሌላም መንገድ ተጠቃሚው ይህን ስምምነት ሲጥስ ወይም ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ተጠቃሚው ስምምነቱን እንደጣሰ ሲጠረጥር ይህንን ስምምነት ወይም የተጠቃሚውን ሰብስክሪፕሽን
ሊያቋርጥ ይችላል፡፡
በአማራጩ፣ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በራሱ ምርጫ የሶፍትዌሩን ፈቃድ ሊያቋርጥ እና/ወይም ተጠቃሚው አገልግሎቱን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል እንዳያገኝ ማድረግ ይችላል፡፡ ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና
መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በዚህ መሠረት ውሉን ወይም ሰብስክሪፕሽኑን ሲያቋርጥ ለተጠቃሚው ሊያሳውቅም ላያሳውቅም ይችላል፡፡ ተጠቃሚው ውሉ ወይም ሰብስክሪፕሽኑ እስከተቋረጠበት (የተቋረጠበትን ቀን ጨምሮ) በአካውንቱ ያልተከፈለን ገንዘብ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል፡፡
ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በማንኛውም ጊዜ ተጠቃሚውን አሳውቆም ሆነ ሳያሳውቅ አገልግሎቶቹንና ይዘቶችን በሙሉም ሆነ በከፊል የመለወጥ፣ የማገድ፣ ወይም የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ይህንን
ሲያደርግ በተጠቃሚውም ሆነ በሌላ በማንኛውም ሦስተኛ ወገን ተጠያቂ አይደረግም፡፡

21. ለውጦች

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በየትኛውም ጊዜና በብቸኝነት ይህን ስምምነት የማዘመን፣ የመከለስ፣ ወይም ስምምነቱ ላይ የመጨመር ወይም በሌላ መልኩ የመለወጥ እንዲሁም በአገልግሎቶቹ አጠቃቀም ዙሪያ አዲስ ወይም ተጨማሪ ድንጋጌዎችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ደንቦችንና ሁኔታዎችን የማካተት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እነዚህ ዝመናዎች፣ ክለሳዎች፣ ጭማሬዎች፣ ለውጦች እና ተጨማሪ ድንጋጌዎች፣ ፖሊሲዎች፣ ደንቦችና ሁኔታዎች ወዲያውኑ ተፈጻሚ መሆን የሚጀምሩ ሲሆን በዚህ ስምምነት ውስጥም የተካተቱ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ ተጠቃሚው ይህንን ስምምነት በየጊዜው በመመልከት የተደረጉትን ለውጦች እንዲከታተል ይመከራል፡፡ ከእነዚህ ለውጦች መካተት በኋላ ተጠቃሚው አገልግሎቶቹን መጠቀም መቀጠሉ የተደረጉትን የትኞቹንም ሆነ ሁሉንም ለውጦች እንደተቀበለ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

22. ማሳወቂያዎች

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ከአገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ለተጠቃሚው ማሳወቂያዎችን በኢሜይል ወይም በአካውንቱ መረጃ ላይ በተጠቀሰው የፖስታ አድራሻ ደብዳቤ በመላክ ያደርሳል፡፡

ለሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚድያ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ማሳወቂያዎችን ለማድረስ [email protected] ላይ ኢሜይል መላክ ይኖርባቸዋል፡፡ ሁሉም ማሳወቂያዎች የተጠቃሚውን ስም፣ የአካውንት ስም፣ አድራሻ፣ የስልክ ቁጥርና ኢሜይል በግልጽ ማካተት አለባቸው፡፡

23. ገዢ ሕግ

ይህ ስምምነት የሚገዛው በኢትዮጵያ ሕጎች ሲሆን ከዚህ ስምምነት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮችን የመዳኘት ብቸኛው ሥልጣን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፍርድ ቤቶች ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተጠቃሚው አገልግሎቶቹን መጠቀም በሌሎች አካባቢያዊ፣ ክልላዊ፣ ብሔራዊ ወይም ዓለም አቀድ ሕጎች ሊተዳደር ይችላል፡፡

Play roulette for both the road and pennsylvania. All the Greece Casinos Available Casino Site Rating Highlight Games Secure Link Terms and Conditions Novibet 5/5 Score Top Performing Casino 2,814+ VISIT CASINO Stoiximan 4. There are some restricted territories, however natcasinosverige.com. For a light snack or meal, you can check out the bar menu that offers starters, sandwiches and pizzas.

error: Content is protected !!
Scroll to Top